dcra

Department of Consumer and Regulatory Affairs
 

DC Agency Top Menu


The DC Business Portal will be unavailable January 10, 8:00pm– Midnight due to scheduled maintenance. We will notify you once maintenance is complete and the application is available. Thank you for your patience.

-A +A
Bookmark and Share

Amharic (አማርኛ)

This page contains information about Department of Consumer and Regulatory Affairs services for Amharic speakers.

የኤጀንሲ ስም፡ የተጠቃሚዎች እና የቁጥጥር ጉዳዮች መምሪያ (Department of Consumer and Regulatory Affairs)

የተልዕኮ መግለጫ ፦ የተጠቃሚዎች እና የቁጥጥር ጉዳዮች መምሪያ (Department of Consumer and Regulatory Affairs) (DCRA) የነዋሪዎችን የአኗኗር ሁኔታ፣ ስራዎቻቸውን እና የኮሎምቢያ አውራጃ ጎብኚዎችን ጤንነት፣ ደህንነት፣ የኢኮኖሚ ፍላጎቶችን እና ጥራትን የኮድ ማረጋገጫን እና የስራ ቁጥጥርን በማረጋገጥ ተልዕኮውን ያስፈፅማል።

አገልግሎቶች፦ DCRA በኮሎምቢያ አውራጃ ውስጥ ግንባታን እና የንግድ ስራን ለመቆጣጠር ሃላፊነት ያለበት መስሪያ ቤት ነው። ኤጀንሲው የተዋሃደ የፈቃድ ማዕከልን ያከናውናል እና ሁሉንም የግንባታ ሰነዶች ከግንባታ ኮዶች እና ከዞን ደንቦች ጋር አግባብ ያለው ስምምነት እንዳላቸው ይገመግማል። ተጠቃሚዎችን ለመጠበቅ፣ DCRA የንግድ ፈቃዶች፣ የሞያ ፈቃዶች፣ እና የልዩ ዝግጅቶች ፈቃዶች፣ የተመዘገቡ ኮርፓሬሽኖች፣ እና ትርፍን ለመቆጣጠር አገልግሎት የሚውሉ የቁጥጥር መለኪያ መሳሪያዎችን ይሰጣል። የግንባታ እንቅስቃሴ፣ የግንባታ ስርዓቶች፣ እና አስፈላጊ ከሆነ የሚከራዩ ቤቶች ምስረታዎች ቁጥጥር ይደረግባቸዋል እና የመኖሪያ ቤት ኮድ ጥሰቶች ይቀንሳሉ።

ዋና ፕሮግራሞች/ የክፍፍል ዝርዝር፦

  •  የዞን መስተዳድር፦ የመሬት እና የህንፃ ፕላኖችን በዞኑ ደንቦች መሰረት መሰራታቸውን ይገመግማሉ። የBZA ትዕዛዛትን እና የዞን ደንቦች ለውጥን በስራ ላይ እንዲውሉ ያደርጋሉ፣ እንዲሁም የዞን ምርመራን ያከናውናሉ።
  •  የፈቃድ ሰጭ ክፈል ፦ የግንባታ፣ የልዩ ምልክት እና የማፍረስ ፈቃዶችን ይሰጣል፣ እንዲሁም የይዞታ ማረጋገጫ ምስክር ወረቀትን እና በመኖሪያ ቤት ውስጥ የመኖር ምስክር ወረቀትን ይሰጣል አዲስ አድራሻም ይመድባል።
  •  የዳይሬክተሩ ቢሮ ፦ ስለ DCRA ደንቦች ክንውን ለፕሬስ እና ለህዝብ መረጃን ይሰጣል። ውስብስብ ጥያቄዎች እና ልዩ ፍላጎቶች ላላቸው ደንበኞች እገዛ ይሰጣል። የመረጃ ማግኘት ነፃነት ህግ (Freedom of Information Act (FOIA)) ጥያቄዎች መረጋገጣቸውን እና የዓለም አቀፍ የDCRA አገልግሎት ውህደት መከናውኑን ያረጋግጣል።
  •  የቁጥጥር ክፍል ፦ በንግድ ስፍራዎች እና ከፍተኛ የመኖሪያ ቤት ባለባቸው ቦታዎች ግንባታዎችን፣ ማሻሻያዎችን፣ እና ጥገናን ይቆጣጠራል። ደረጃቸውን ላልጠበቁ፣ ህገወጥ ለሆኑ እና በአደገኛ ሁኔታ ላይ ላሉ የመኖሪያ ቤቶች አቤቱታ ምላሽ ይሰጣል እና ማስተካከያዎችን ያፀድቃል።
  •  በስራ ላይ የሚያውል ቢሮ፦ ጽዱ ላልሆኑ ህንፃዎች አጋጅ ቦርድ (Board of Condemnation of Insanitary Buildings (BCIB)) ህንፃዎችን ይመረምራል፣ ስለዚህ ህንፃዎች መቼ መታገድ፣ መጠገን፣ ወይም መፍረስ እንዳለባቸው ይወስናሉ ። በተጨማሪም ባለቤቱ መኖሪያ ቤቱን ማስተካከል በሚሳነው ጊዜ ወይም የህንፃ ኮድን ጥሰቶችን በሚያከናውን ጊዜ እርምጃን ይወስዳል። ለባለቤቱ ካሳወቀ በኋላ፣ DCRA ጥገናዎችን ማከናወን ይችላል እና ባለቤቱን ያስከፍላል።
  •  የንግድ ፈቃድ፦ የንግድ ፈቃድ ክፍል ለአዲስ ንግዶች ፈቃዶችን ይሰጣል እና ቀድሞ ለተቋቋሙ የንግድ ስራዎች ፈቃዶችን ያድሳል።
  •  ቦታ የመያዝ እና የሞያ ፈቃዶች ፦ ለሚከተሉት ሞያዎች ፈቃድ ይሰጣል፦ አካውንቲንግ፣ አፕሬዛል፣ አርክቴክቸር እና የውስጥ ዲዛይን፣ የአስቤስቶስ ስራ፣ የአትሌት ኤጀንት፣ የፀጉር መቁረጥ፣ የቦክሲንግ እና ነፃ ትግል፣ ኮስሜቶሎጂ፣ ኤሌክትሪሻን፣ የቀብር ማስፈፀም፣ የቧንቧ ስራ፣ ሪል ስቴት፣ እና የአየር ማረጋጊያ፣ እና ስትሪም ኢንጂነሪንግ።

የትርጉም አገልግሎቶች፦ በእርስዎ ቋንቋ ተጨማሪ እገዛን ለማግኘት እባክዎ ቢሮአችንን በስልክ ቁጥር (202) 442-8799 ያነጋግሩ። ወደ ቢሮአችን ሲደውሉ ወይም በአካል ቢሮአችንን ሲጎበኙ፣ ሰራተኞቻችን በቀጥታ ወደ የትርጉም አገልግሎት እንደሚያገናኙዎት እና እገዛ እንደምናደርግልዎ እርግጠኛ ነን።

የምንገኝበት አድራሻ መረጃ፦
የተጠቃሚዎች እና የቁጥጥር ጉዳዮች መምሪያ (Dept. of Consumer & Regulatory Affairs)
1100 4th Street SW
Washington, DC 20024
ቢሮ፦ (202) 442-4400
www.dcra.dc.gov